መሬትን ማስለቀቅ (Expropriation or Eminent Domain)

በሃገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ መሬትን ለልማት እየተባለ ከባለይዞታዎች/ባለቤቶች ካሣ እየተከፈለ ማስነሳት በጣም የቆየ ታሪክ አለው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነን ንጉሥ ላሊበላ አስራ አንዱን አብያተ ክርስቲያናት የምድርን ሆድ ቦትርፎ ሲያንጻቸው በወቅቱ የመሬቱ ባለቤቶች ለነበሩት ሰዎች የመሬቱን ዋጋ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን ታሪክ በገድለ ቅዱስ ላሊበላ እንደሚከተለው ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ [ገድሉ የተጻፈው ከላሊበላ ሞት ሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ነው፡፡] “… ወውእተኒ :… Read More መሬትን ማስለቀቅ (Expropriation or Eminent Domain)

ከ”መሬት ላራሹ” በፊት የታወጀ “መሬት ላራሹ” “ሰብእ ሐራ፣ ወምድር ገባር”

“ሰብእ ሐራ፣ ወምድር ገባር” ወደ አማርኛ ሲመለስ “ሰው ነጻ ነው፣ መሬት ግብር ነው” ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጎም “man is free, land is tributary.” የሚል ትርጉም አለው፡፡ ይህን የተናገረው ማን ነው? የስድሳዎቹ ትውልድ እንዳትሉ፡፡ ደግሞ ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄዳችሁ ፈረንጅ እንዳትጠቅሱልኝ፡፡ ይህ የአንድ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አዋጅ ነው፡፡ የዐፄ ዘድንግል አዋጅ ነው (1595-96 ዓ.ም)፡፡ ዐፄው ይህን አዋጅ ያወጀበት… Read More ከ”መሬት ላራሹ” በፊት የታወጀ “መሬት ላራሹ” “ሰብእ ሐራ፣ ወምድር ገባር”

አዲሱ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 The New Commercial Registration and Business Proclamation No 980/2016

አዲሱ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ይኸውላችሁ፡፡ አዋጁ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል፡፡ ከነዚህ መካከል አንደኛው እስካሁን ድረስ በሀገራችን በተግባር ሲሠራበት የነበረው ነገር ግን ምንም ዓይነት የሕግ እውቅና የሌለውን የፍራንቻይዝ ስምምነት እውቅና ሰጥቶ ብቅ ብሏል፡፡ ሌሎች ነገሮችም ይዟል፤ ሁሉንም ለማየት እነሆ፡፡ the-new-commercial-registration-and-business-licensing-proclamation-no-980_2016  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማስፈጸሚያ መመሪያ Manner of Relinquishing Shareholdings of Foreign Nationals of Ethiopian Origin in a Bank and Insurer, Guideline No FIS/01/2016

ይህ መመሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 22፣ 2009 ዓ.ም (Vovember 1, 2016) ዜግነታቸው የሌላ አገር የሆኑ  ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ባንኮች እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ያላቸውን የአክስዮን መብት ለመቆጣጠር ያወጣው መመሪያ ነው፡፡ በዚህ ማስፈጸሚያ መመሪያ መሠረት፡- ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዜግነታቸው የሌላ አገር ለሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክስዮኖች ያላቸውን ትርፍ (dividend) እስከ ጁን 30፣ 2016 መክፈል እንዳለባቸው… Read More የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማስፈጸሚያ መመሪያ Manner of Relinquishing Shareholdings of Foreign Nationals of Ethiopian Origin in a Bank and Insurer, Guideline No FIS/01/2016

ብድር – ሉአላዊነት – ልማት

በቀ/ኃ/ሥ ዘመን በአንድ ወቅት የኢጣሊያ መንግሥት 35 ሚሊዮን ብር ብድር ይሰጣል፡፡ ብድሩ መጽደቅ ስለነበረበት በሕግ መምሪያ ም/ቤት በኩል ያለምንም ችግር ጸደቀ፡፡ ቀጥሎ ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቀረበ፡፡ (የሕግ መወሰኛ ም/ቤቱ የላይኛው የም/ቤት መዋቅር ነበር፡፡) የሕግ መወሰኛ ም/ቤቱ ሰባት አባላት ያሉት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጉዳዩን አጣርቶ እንዲያቀርብ ያዛል፡፡ በዚህ መሠረት የብድር ውሉ ሲመለከቱት አንቀጽ 10 ስለ… Read More ብድር – ሉአላዊነት – ልማት

ዐፄ ቴዎድሮስና ግብር

ዐፄ ቴዎድሮስና ግብር   ሰኔ 8 ቀን 1858 ዓ.ም   ጋፋት   ከ160 ዓመት በፊት ልክ በዛሬ ዕለት ግርማዊ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ በመሠረቱት የኢንዱስትሪ መንደር ባለችው ጊዜያዊ ማረፊያቸው ውስጥ ሆነው ከእንግሊዛዊው ሆርሙዝድ ረሳም ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ ነበር፡፡ ራሳም በወጣቱ አስተርጓሚ ደስታ አማካኝነት በተለይ በእንግሊዝ አገር ግብር (Tax) እንዴት እንደሚጣልና እንደሚሰበሰብ… Read More ዐፄ ቴዎድሮስና ግብር

የፍትሕና ሕግ ሥርዓት ምርምር ተቋም ከሰሞኑ አንድ መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ17 የሕግ ዘርፎች የተመረጡ ውሳኔዎች ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዕትሙ የአዋጆችና የደንቦች መጠቁም (Index) አካቷል፡፡ መጠቁሙ አዋጆችን በዘርፍ በዘርፍ እንዲሁም ዝርዝራቸውን ከ1987-2005ዓ.ም ድረስ ያለውን ያካትታል፡፡ መጽሐፉ እነሆ፡፡ ወይም ይህን ማስፈንጠሪያ ተከትላችሁ ታገኙታላችሁ፡፡ http://www.africanlawlibrary.net/newsletter Etlex_Volume1

ይህን ያውቁ ኖሯል? (የበጀት ዓመት መጀመሪያ)

እስከ 1951 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ የበጀት ዓመት የሚጀመረው በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መስከረም 1 ቀን ነበር፡፡ ነገር ግን አዋጅ ቁጥር 162/1951 (18ኛ ዓመት፣ ቁጥር 13) ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የበጀት ዓመቱ የሚጀመረው ሐምሌ 1 ቀን እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የሕግ ት/ቤቶችና ቋንቋ በኢትዮጵያ–ካልአይ ክፍል (የመጨረሻ)

ሕግ ትምህርትና አማርኛ በአሁኑ ወቅት የሕግ ትምህርት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ከ/ት/ተ) እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በተለይ ከ1994 ዓ.ም ወዲህ የሕግ ትምህርት ቤቶች በመንግሥትም ሆነ በግል ከ/ት/ተ ዘንድ በመደበኛ፣ በማታ፣ በተከታታይና በርቀት መርኀ-ግብር እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የሕግ ት/ቤቶች ቁጥራቸውም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡ የቁጥሩ ማደግ የራሱ የሆነ በጎ እና አሉታዊ ጎኖች ቢኖሩትም ከሁለት ዓመታት ወዲህ ግን የሕግ ትምህርት… Read More የሕግ ት/ቤቶችና ቋንቋ በኢትዮጵያ–ካልአይ ክፍል (የመጨረሻ)