ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ ይችን ጦማር እነሆ ብያለሁ፡፡ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ — የሴቶች መብት ተሟጋች በሀገራችን የሴቶችን መብት ለማስከበር ከተንቀሳቀሱት እናቶቻችን መካከል ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ወ/ሮ ስንዱ የብዙ ሙያ ባለቤት ናቸው፡፡ ወ/ሮ ስንዱ በቀ/ኃ/ሥ ዘመን የመጀመሪያዋ የሕግ መምሪያ ም/ቤት አባልና የም/ቤቱም ምክትል ፕሬዚዳንት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ታዲያ በዚህ በም/ቤት ቆይታ ዘመናቸው ለሴቶች መብት… Read More ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

የግሪር ችሎት (The Greer Case)

  የመጽሐፉ ርዕስ፡- የግሪር ችሎት (The Greer Case) ደራሲ፡- David W. Peck ተርጓሚ፡- አብነት ሽመልስ የገጽ ብዛት፡- 164 ዋጋ፡ 45.00 የታተመበት ዘመን፡- 1955 እ.ኤ.አ (ትርጉም 2007 ዓ.ም) ይህ መጽሐፍ በአሜሪካን አገር በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ለፍርድ ቤት የቀረበን አንድ ጉዳይ የፍርድ ሂደት የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡ ጉዳዩ በወቅቱ ድፍን አሜሪካን ያነጋገረ፣ የሁሉንም ቀልብ የሳበ ነበር፡፡ ለፍርድ… Read More የግሪር ችሎት (The Greer Case)

ሕግና አወጣጥ እና ችግሮቹ

የቅርስ አዋጅ መቼም ሕግ ሲወጣ ሁሉም ነገር ፍጹም ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ መሠረታዊ የሕግ አወጣጥ መርህ እንዳለ ሆኖ የትርጉም ችግርና ትክክለኛ ቃላትን መጠቀም በሕግ አወጣጥ ሂደት እንዲሁ በዋዛ የሚታዩ ነገሮች አይደሉም፡፡ ታላቁ መጽሐፍ “ፊደል ይገድላል” አይደል የሚለው፡፡ ሕግ ሲወጣ ሥርዐተ ነጥቡ፣ ቃላቱ፣ ብዙና ነጠላ ቁጥሮች፣ ርዕስ አቀራረጹ፣ ቃላት አሰካኩ፣ መግቢያ /መንደርደሪያ/ ሐረጉ፣ ትርጉሙ (አማርኛና እንግሊዝኛ ወይም… Read More ሕግና አወጣጥ እና ችግሮቹ

በእንተ ታሪክ

እስኪ ስለ ታሪክ የተነገሩ ሦስት አባባሎችን ላስታውሳችሁ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል፡፡” “ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችን ነው፡፡” “ታሪክ ይገለበጣል፡፡” ዛሬ የማካፍላችሁ ታሪክ የተገለበጠበትን አንድ ሁነት ነው፡፡ ነፍሳቸውን ይማርና አቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” (1ኛ መጽሐፍ) በሚለው የታሪክ ድርሳናቸው ላይ የሚከተለውን ታሪክ በጥሩ አማርኛ አስፍረውት እናገኛለን፡፡ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ እነ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝና፣ አሜሪካና ኢጣሊያ ጦርነቱን… Read More በእንተ ታሪክ

ኑ! ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እንከላከልለት!

የእሁድ፣ ግንቦት 29፣ 2009 ዓ.ም የሪፖርተር ጋዜጣ የፊት ገጽ እንዳስነበበን ከሆነ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት “ኢ.ቢ.ሲ የቆመለትን ዓላማ የማይወክል፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት (የሥራ አስፈጻሚው አባላት) የሚታዘዝ ነው፤ የሕዝብ ሚዲያ መሆን አልቻለም፤ ዝግጅቶቹ አሰልቺ ናቸው፡፡” በማለት ብዙ ትችቶችን ሰንዝረው ኢቢሲን ደህና አድርገው ወቅጠው አስጥተውታል፡፡ (ግን እስከዛሬ የት ሄደው ነው?) የምር ግን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጨዋ ነው፤… Read More ኑ! ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እንከላከልለት!

መጽሐፈ አክሱም፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ መጽሐፍ እጃችን ገብቷል፡፡ ላውጋችሁ፡፡ መጽሐፈ አክሱም፡፡ መቼም ዘዋሪ ነኝና ሰሞኑን በጎግል መንደር ሳልፍ ከመጽሐፈ አክሱም ጋር ተያየን፡፡ መጀመሪያ በደንብ ስለማንተዋወቅ ልንተላለፍ ነበር፡፡ ግን “ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ” ነውና በደንብ ስንተያየ ተዋወቅን፤ በፍቅር ተቃቀፍን፡፡ እኔም ቸኮልኩና እያገላበጥኩ እየሳምኳት ወደ ቤቴ ይዣት ገባሁ፡፡ ጥቂት ወየብ ብላለች፤ ንግግሯ ሁሉ ግማሽ በግማሽ ፈረንሳይኛ ነው፤ ግማሹ… Read More መጽሐፈ አክሱም፡፡