ሕግና አወጣጥ እና ችግሮቹ

የቅርስ አዋጅ

መቼም ሕግ ሲወጣ ሁሉም ነገር ፍጹም ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ መሠረታዊ የሕግ አወጣጥ መርህ እንዳለ ሆኖ የትርጉም ችግርና ትክክለኛ ቃላትን መጠቀም በሕግ አወጣጥ ሂደት እንዲሁ በዋዛ የሚታዩ ነገሮች አይደሉም፡፡ ታላቁ መጽሐፍ “ፊደል ይገድላል” አይደል የሚለው፡፡ ሕግ ሲወጣ ሥርዐተ ነጥቡ፣ ቃላቱ፣ ብዙና ነጠላ ቁጥሮች፣ ርዕስ አቀራረጹ፣ ቃላት አሰካኩ፣ መግቢያ /መንደርደሪያ/ ሐረጉ፣ ትርጉሙ (አማርኛና እንግሊዝኛ ወይም እንደየአግባቡ ሌሎቹ ቋንቋዎች)፣ ጽንሰ-ሃሳቡ፣ ወዘተ. በጥንቃቄ ሊሠራ ይገባዋል፡፡ አለዚያ ግን ሕጉ ብዙ ችግሮችን አዝሎ መብቶችና ነጻነትን ሊያጣብብ፣ ግዴታዎችን ሊያበዛ፣ ይችላል፡፡ በተለይ አሁን አሁን በሚወጡት ሕግጋት አወጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ይመስላል፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ስህተቶች የሕግ ጽንሰ ሃሳብ ያለው ሰው ያያቸው አይመስሉም፡፡ ሰሞኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 210/1992 ስመለከተው ነበር፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 18፣ 20፣ 21፣ 26 እና 27 ሥር የሚታዩት ችግሮች ከዚህ በታች አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

  1. አንቀጽ 18፡– የርዕሱና የመግቢያ ዐ.ነገሩ ትርጉም የተለያየ ነው፡፡ ርዕሱ “ቅርስ ባለይዞታ ግዴታዎች” ሲል መግቢያ ዐ.ነገሩ ደግሞ “…ቅርስን በባለቤትነት የያዘ ሰው…” ይላል፡፡ ይዞታ እና ባለቤትነት ይለያያሉ፤ ባለቤትነት በጣም ሰፊ የሆኑ መብቶችን የሚያካትት ቃል ሲሆን ይዞታ ደግሞ ጠበብ ያለ ትርጉም ያለው በባለቤትነት መብት ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ አንድ የሕግ አውጭ እነዚህ ሁለት የተለያዩ ጽንሰ-ሃሳቦች ይስታል ተብሎ መገመት ከባድ ነው፤ ግን ሆነ፡፡

አንቀጽ 18 እንግሊዝኛው ደግሞ የአማርኛው ግልባጭ ነው፤ ርዕሱ ስለ ባለቤትነት የሚናገር ሲሆን መግቢያው ደግሞ ስለ ይዞታ ይናገራል፡፡

በትክክለኛው መሆን ያለበት ግን ርዕሱም ሆነ መግቢያው ስለ ባለቤትነት ቢቀመጡ ኖሮ ነው፡፡ ማለትም የአማርኛው ቅጅ ርዕሱ “ይዞታ” የሚለው “ባለቤትነት”፤ የእንግሊዝኛው ቅጅ መግቢያው “possesses” የሚለው “owns” መሆን አለበት፡፡

  1. አንቀጽ 20፡- አማርኛውና እንግሊዝኛው ተቃራኒ ነገሮች ናቸው፡፡ አማርኛው ርዕሱ “በይዞታ እንዲጠቀምበት በተሰጠው መሬት…” የሚል ሲሆን እንግሊዝኛው ደግሞ “…land given in usufruct” በአማርኛ ሲተረጎም “በኪራይ እንዲጠቀምበት…” ይላል፡፡ “ይዞታ” እና “ኪራይ” ፍጹም የተለያዩ ጽንሰ-ሃሳቦች ናቸው፡፡ የመሬት ይዞታ በዋናነት ከመንግሥት የሚገኝ ወይም በውርስ ወይም በስጦታ ሊገኝ የሚችል ነው፡፡ ኪራይ ግን ከሁለት ሰዎች የውል ግንኙነት የሚመነጭ ነው፡፡ ስለዚህ ይዞታና ኪራይ ፍጹም የተለያዩ በመሆናቸው በእንግሊዝኛ “…land given in usufruct” የሚለው መሆን ያለበት “…land holding” ነው፡፡
  2. አንቀጽ 21፡- የአማርኛው ርዕሱ ቅርስን ስለማንቀሳቀስ ሲል ንዑስ አንቀጾቹ ደግሞ የማይንቀሳቀስና የሚንቀሳቀስ ቅርሶችን ማንቀሳቀስ የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች የሚደነግጉ ናቸው፡፡ የእንግሊዝኛው ርዕስ እና ንዑስ አንቀጾች የሚደነግጉትም ከአማርኛው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ነገር ግን በአማርኛ “ስለማንቀሳቀስ” የሚለው ቃል በእንግሊዝኛው ርዕስና በንዑስ አንቀጾቹ ሥር “Removal” ተብሏል፤ ነገር ግን የአማርኛውና የእንግሊዝኛው ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም የላቸውም፡፡ በአማርኛ “ማንቀሳቀስ” የሚለው በእንግሊዝኛው “Movement” ማለት ነው፡፡

Removal እና Movement የተለያየ ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው፡፡ Removal አንድን አካል ካለበት ቦታ /ሥልጣን/ ማንሳት፣ ማስወገድ ማለት ነው፡፡ Removal of Judges እንዲል (የፌዴራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቀ. 25/88 አንቀጽ 28)፡፡ Removal የሚለው ቃል በሁሉም ሕጎቻችን ውስጥ ወጥ የሆነ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ Movement ማለት ደግሞ አንድ አካል በራሱ ወይም በሰው አጋዥነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የቅርስ አዋጅ ቁ. 209/2000 አንቀጽ 21 ርዕሱ እና ንዑስ አንቀጾቹ የሚደነግጉት ቅርሶች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚንቀሳቀሱበትን አግባብ የሚደነግግ ስለሆነ Movement እንጅ Removal ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ የአንቀጽ 21 እንግሊዝኛው ርዕስ መሆን ያለበት Removal of Cultural Heritages ሳይሆን “Moving Cultural Heritages” ነው፡፡ በተመሳሳይ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ሥር removed የሚለው ቃል moved በሚለው፣ እንዲሁም በንዑስ አንቀጽ (2) ሥር removing የሚለው ቃል moving በሚለው ቃል መስተካከል አለበት፡፡

  1. አንቀጽ 26፡- ይህ አንቀጽ የሚደነግገው ደግሞ በሕገ-ወጥ መንገድ በውጭ የሚገኝ የኢትዮጵያ ቅርስ ስለማስመለስ ነው፡፡ የአማርኛው ርዕስ “በሌላ አገር ስለሚገኝ ቅርስ” ይላል፡፡ ነገር ግን ይህ ርዕስ የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት ሙሉ በሙሉ አይገልጽም፡፡ በትክክል ሊገልጽው የሚችለው የርዕሱ አቀራረጽ “በሌላ አገር የሚገኝን ቅርስ ስለማስመለስ” ተብሎ ቢጻፍ ነው፡፡
  2. አንቀጽ 27፡- ይህ አንቀጽ የሚደነግገው ደግሞ አንድን ቅርስ ከኢትዮጵያ ውጭ ማውጣት ስለመከልከሉ እና ስለ ልዩ ሁኔታው ነው፡፡ የአንቀጹ ርዕስ አማርኛውና እንግሊዝኛው ልዩነቶች ይታዩበታል፡፡

ታዲያ የነዚህ ሁሉ ችግሮች አንደኛው መንስኤ የሕግ አርቃቂው ይመስላል፡፡ ሕግ እንዲያረቅቁ ኃላፊነት የሚሰጣቸው ሰዎች የአቅም ውስንነት ይታይባቸዋል፡፡ ሕግ የማርቀቅ ሥራ ዝቅተኛ የሚባል ተከፋይ ስለሆነ ከዚያ ቦታ ላይ የሚሠሩ ብቁ ሰዎችን ማግኘት አይቻልም፡፡ ሥራውን በሚገባ ሲለምዱት ደግሞ ጥለውት ከፍ ወደሚል ቦታ ስለሚሄዱ የሕግ አወጣጥ ችግሩ እንዳለ ይቆያል፡፡ በርግጥ ሕግ አውጭው ከአርቃቂው አምልጠው የሚሄዱ ስህተቶችን ማረም ይገባዋል፡፡ መፍትሔውም ሕግን የሚያረቅቁ ሰዎች ከፍተኛ ልምድ ያላቸው፣ ቢቻል ከሕግ ውጭ ሌሎች ሙያዎችን የሚያውቁ፣ የተማሩ፣ የሥራ ደረጃውም ከፍ ያለ ቢሆን ችግሩን በከፍተኛ ደረጃ ማቃለል ይቻላል፡፡

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s