በእንተ ታሪክ

እስኪ ስለ ታሪክ የተነገሩ ሦስት አባባሎችን ላስታውሳችሁ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል፡፡” “ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችን ነው፡፡” “ታሪክ ይገለበጣል፡፡” ዛሬ የማካፍላችሁ ታሪክ የተገለበጠበትን አንድ ሁነት ነው፡፡ ነፍሳቸውን ይማርና አቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” (1ኛ መጽሐፍ) በሚለው የታሪክ ድርሳናቸው ላይ የሚከተለውን ታሪክ በጥሩ አማርኛ አስፍረውት እናገኛለን፡፡ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ እነ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝና፣ አሜሪካና ኢጣሊያ ጦርነቱን… Read More በእንተ ታሪክ

ኑ! ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እንከላከልለት!

የእሁድ፣ ግንቦት 29፣ 2009 ዓ.ም የሪፖርተር ጋዜጣ የፊት ገጽ እንዳስነበበን ከሆነ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት “ኢ.ቢ.ሲ የቆመለትን ዓላማ የማይወክል፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት (የሥራ አስፈጻሚው አባላት) የሚታዘዝ ነው፤ የሕዝብ ሚዲያ መሆን አልቻለም፤ ዝግጅቶቹ አሰልቺ ናቸው፡፡” በማለት ብዙ ትችቶችን ሰንዝረው ኢቢሲን ደህና አድርገው ወቅጠው አስጥተውታል፡፡ (ግን እስከዛሬ የት ሄደው ነው?) የምር ግን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጨዋ ነው፤… Read More ኑ! ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እንከላከልለት!

መጽሐፈ አክሱም፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ መጽሐፍ እጃችን ገብቷል፡፡ ላውጋችሁ፡፡ መጽሐፈ አክሱም፡፡ መቼም ዘዋሪ ነኝና ሰሞኑን በጎግል መንደር ሳልፍ ከመጽሐፈ አክሱም ጋር ተያየን፡፡ መጀመሪያ በደንብ ስለማንተዋወቅ ልንተላለፍ ነበር፡፡ ግን “ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ” ነውና በደንብ ስንተያየ ተዋወቅን፤ በፍቅር ተቃቀፍን፡፡ እኔም ቸኮልኩና እያገላበጥኩ እየሳምኳት ወደ ቤቴ ይዣት ገባሁ፡፡ ጥቂት ወየብ ብላለች፤ ንግግሯ ሁሉ ግማሽ በግማሽ ፈረንሳይኛ ነው፤ ግማሹ… Read More መጽሐፈ አክሱም፡፡