መሬትን ማስለቀቅ (Expropriation or Eminent Domain)

በሃገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ መሬትን ለልማት እየተባለ ከባለይዞታዎች/ባለቤቶች ካሣ እየተከፈለ ማስነሳት በጣም የቆየ ታሪክ አለው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነን ንጉሥ ላሊበላ አስራ አንዱን አብያተ ክርስቲያናት የምድርን ሆድ ቦትርፎ ሲያንጻቸው በወቅቱ የመሬቱ ባለቤቶች ለነበሩት ሰዎች የመሬቱን ዋጋ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን ታሪክ በገድለ ቅዱስ ላሊበላ እንደሚከተለው ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ [ገድሉ የተጻፈው ከላሊበላ ሞት ሁለት መቶ ዓመታት በኋላ ነው፡፡]

“… ወውእተኒ : ምድረ : ኀበ : ገብረ : አብያተ : ክርስቲያናት : ተሣየጡ : በወርቁ : እምኀቤሆሙ : ለእለ : ይኴንንዎ : ለይእቲ : ምድር : እንዘ : ይፈደፍድ : ኂሩተ፡፡ ወለእመሰ : ፈቀደ : ከመ : ይንሣእ : መኑ : እምከልኦ : ለንጉሥ:: …”[1]

(የዚህን ንባብ ትርጉም ግዕዝ የሚችሉ ሰዎች ቢረዱን ከፍ ያለ ደስታ ይሰማናል፡፡) ገጸ ንባቡን ስንረዳው ግን ላሊበላ እነዚያን አብያተ ክርስቲያናት ሲሠራ ለመሬት ተነሺዎች ገንዘብ መክፈሉን ይነግረናል፡፡ በመቀጠልም ደራሲው “ንጉሡ መሬቱን እንዲሁ (ያለገንዘብ) ቢወስድስ ማን ይከለክለዋል?” በማለት በጊዜው የነበረውን አስተሳሰብ በተጠየቅ ይነግረናል፡፡ በርግጥም ማንም ሊከለክለው አይችልም ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የንጉሡን ደግነት አብሮ ይገልጽልናል፡፡ እንደዚሁም በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት መሬትን እንደፈለጉ የማድረግ ሙሉ ሥልጣን ያላቸው ሲሆኑ ንጉሥ ላሊበላ ግን ለነዚያ ገበሬዎች ካሣ ከፈላቸው፡፡

ለምሳሌ ብንወስድ ንጉሥ ዐምደ ጽዮን  “በንጉሥ ምድር የት ትደርሳላችሁ?” በማለት ጻድቁ አቡነ አሮንን እንዳሰቀየው የጻድቁ ገድል ሲናገር የዐምደ ጽዮን ልጅ የሆነው ንጉሥ ሠይፈ አርዕድ ደግሞ “እግዚአብሔር ሁሉንም መሬት ለኔ ሰጠኝ” ማለቱን የታሪክ ድርሳናት ያወሱናል፡፡ ከዚህ አንጻር ስንመለከተው የንጉሥ ላሊበላ ድርጊት ከዘመኑ እጅግ የፈጠነ ወይም ተራማጅ ነበር፡፡ ላሊበላ በግዛቴ ውስጥ የፈለኩትን ባደርግ ማንም አያግደኝም ከማለት ይልቅ ለመሬት ተነሺዎች /ለባለቤቶቹ/ የመሬቱን ግምት ከፈለ፡፡

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በተመለከተ የበውቀቱ ሥዩምን ሥም ማንሳት ተገቢ ባይሆንም፣ “ከአሜን ባሻገር” በሚለው ድርሰቱ ገጽ 39 ላይ ገድለ ቅዱስ ላሊበላን ጠቅሶ ንጉሡ ለመሬት ተነሺዎች ካሣ መክፈሉን ተመልክቶታል፡፡

[1] ፔሩሾን ያሳተመው ገድለ ቅዱስ ላሊበላ፣ ገጽ 57፤ Tadesse Tamirat, Church and State, p. 98፤ Pankhurst, The Ethiopian Royal Chronicles, ገጽ 13

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s