ከ”መሬት ላራሹ” በፊት የታወጀ “መሬት ላራሹ” “ሰብእ ሐራ፣ ወምድር ገባር”

“ሰብእ ሐራ፣ ወምድር ገባር”

ወደ አማርኛ ሲመለስ “ሰው ነጻ ነው፣ መሬት ግብር ነው” ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጎም “man is free, land is tributary.” የሚል ትርጉም አለው፡፡

ይህን የተናገረው ማን ነው? የስድሳዎቹ ትውልድ እንዳትሉ፡፡ ደግሞ ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄዳችሁ ፈረንጅ እንዳትጠቅሱልኝ፡፡

ይህ የአንድ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ አዋጅ ነው፡፡ የዐፄ ዘድንግል አዋጅ ነው (1595-96 ዓ.ም)፡፡ ዐፄው ይህን አዋጅ ያወጀበት ምክንያት በወቅቱ የጉልበት ብዝበዛ ለሚደርስባቸው፣ መሬት የማግኘት መብት ለተነፈጋቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ያወጣው አዋጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሰውነቱ ነጻ ነው፤ እንደ ነጻነቱ ጥሮ ግሮ ለራሱ እንጅ ጉልበቱን ለመሬት ባላባቶች መገበር አይገባውም ብሎ ያወጀበት ነው፡፡ ሰው ሊገብር የሚገባው በተሰጠው ንብረት (መሬት) ላይ ከሚያኘው ምርት እንጅ ጉልበቱን አይደለም ብሎ ያወጀበት ነው፡፡ ዜጎች መሬት የማግኘት የዜግነት መብት አላቸው ብሎ በአዋጅ ያጸናበት ነው፡፡ ይህም ተራ አርሶ አደሮችን ከጌቶቻቸው ጋር እኩል እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡

ለዚህም ነው ከ”መሬት ላራሹ” በፊት የታወጀ “መሬት ላራሹ” ያልኩት፡፡

ታዲያ ምን ይሆናል፣ ይህ አዋጅ መጥፊያው ሆነ፡፡

ይህን አዋጅ በማወጁ ዜጎች የመሬት ባለቤት በመሆናቸው የራሱ ወታደሮችና ራስ ዘሥላሴ (በቅጽል ሥሙ “ዘሦ” የሚባለው) አመጹበት፡፡ ከዚያም መሀል ደምቢያ ጦርነት ሆነና ዐፄ ዘድንግልን ላይ አንገቱን በጎራዴ ቀንጥሰው ጣሉት፡፡

ውጤቱም ባላባት ጉልበት መበዝበዙን ቀጠለበት፤ እንደ ሐምሌ መብረቅ የክብር ብልጭታ አግኝቶ የነበረው ዜጋ መልሶ ድርግም አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡- ዜጎች የተባሉት መሬት የሌላቸው፣ ለጌቶቻቸው በማገልገል የሚኖሩ ሰዎችን ለመግለጽ የታሪክ ድርሳናት የተጠቀሙበት ቃል ነው፡፡

ምንጭ፡- Donald Crummey, Land and Society in the Chrisitan Kingdom of Ethiopia: 13th to 20th C, pp.63-66.

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s