ዐፄ ቴዎድሮስና ግብር

ዐፄ ቴዎድሮስና ግብር

 

ሰኔ 8 ቀን 1858 ዓ.ም

 

ጋፋት

 

ከ160 ዓመት በፊት ልክ በዛሬ ዕለት ግርማዊ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ በመሠረቱት የኢንዱስትሪ መንደር ባለችው ጊዜያዊ ማረፊያቸው ውስጥ ሆነው ከእንግሊዛዊው ሆርሙዝድ ረሳም ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ ነበር፡፡ ራሳም በወጣቱ አስተርጓሚ ደስታ አማካኝነት በተለይ በእንግሊዝ አገር ግብር (Tax) እንዴት እንደሚጣልና እንደሚሰበሰብ ለጃን ሆይ ሲያብራራለት ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ግርማዊነታቸው ከልባቸው ከትከትከት ብሎ እየሳቁ (የቁጭትና የንዴት ሳቅ እንደሆነ መንፈሱ ይናገራል) “የሃገሬ ሰዎች [ግብር ክፈሉ ብላቸው] በገንዘባቸው ከመነገድ ወይም ለኔ (ለመንግሥቴ) ከመገበር ይልቅ ወዲያውኑ ገንዘባቸውን መሬት ውስጥ ነው የሚቀብሩት፡፡” በማለት የሀገራቸው ህዝብ ግብር ለመክፈል ያለውን ዝቅተኛ አስተሳሰብ ልብ በሚነካ ንግግር መለሱለት፡፡

 

በመቀጠልም አቶ ራሳም በእንግሊዝ አገር በበቅሎዎችና በወንድ አገልጋዮች (ባሮች) ላይ ስለሚሰበሰበው ግብር ሲያስረዳ፤ ግርማዊነታቸው ደግሞ “አቶ ራሳም፣ ኢትዮጵያውያንን አታውቃቸውም፤ በበቅሎዎች፣ በፈረሶችና በቤት እንስሶች ላይ ግብር ብጥል፣ አንድም ሰው [ፈረሱን ወይም በቅሎውን] አይጋልብም ነበር፤ እናም እያንዳንዱ ሰው የራሱ አገልጋይ (ባርያ) ይሆን ነበር” በማለት የቁጭት መልስ መለሱለት፡፡

ምንጭ፡- Hormuzd Rassam, Narrative of the British Mission to Theodore, King of Abyssinia, 1869, Volume II, pp. 131-132

 

ከዘመነ ቴዎድሮስ በኋላ ለግብር ያለን አመለካከትና ግብር የመክፈል ባሕል ከብዙ ዓመታት በኋላ እንኳ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዳልተስተካከለ የነገረን ደግሞ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ “መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር” በሚለው ድርሰቱ ውስጥ ነው፡፡ በርግጥ አሁንም ከዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ገና እንዳልተላቀቅን ይታወቃል፡፡ ከእንስሳት ላይ የሚሰበሰብ ግብርን በተመለከተ ደግሞ ታሪክ እንደሚዘክረን ከሆነ ዐፄ ምኒልክ በዘመናቸው የተበደሩትን የውጭ ብድር ለመክፈል ከእያንዳንዱ ግለሰብ የጋማና የቀንድ ከብት ሃብት ላይ “የጭራ ብር” ጥለው ብድሩን ከፍለዋል፡፡ ይህን ታሪክ ሌላ ጊዜ እነግራችዋለሁ፡፡

 

 

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s