በማንበብ አትሞላም ባለማንበብ አትጎድልም !!

(አሌክስ አብረሃም )

‹‹ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ›› የሚሉት ‹ቀልድ› ያስቀኛል ! እንደውም ጠብታ ውሃ በባዶ እቃ ውስጥ የምታሰማው የመንቦጫረቅ ድምፅ ይመስለኛል መፎክር!! ማንበብ ሲጀመር ሙሉ አያደርግም ….በሰው ልጅ የሂወት ሂደት ውስጥ ‹ሙሉነት …መሙላት › የሚባል ጉዳይ የለም እንደውም ማንበብ ሳይሆን የእድሜ ስፍር ብቻውን ሙሉ እንደሚያደርግ ለማወቅ ሩቅ ሳትሄዱ አባባሉን መውሰድ በቂ ነው ‹‹ እከሌ ሙሉ ሰው ሆነ ›› ማለት ለአቅመ አዳም ደረሰ ማለት ነው… ሴትም ከሆነች ለትዳር ደረሰች (አንዳንድ አካባቢወች እከሊት ሙሉ ሰው ሆነች የሚባለው ልጅቱ የወር አበባ ማየት ስትጀምር ነው)

ሙሉነት አዋቂነትን ለመግለፅ ከሆነ ለማወቅ መሙላት አያስፈልግም ያውም በንባብ መሙላት እንደትልቅ ብቃት መታየቱ ይገርመኛል እኔ ማንም ሰው ቢያነብ ባያነብ ግድ አይሰጠኝም እንደውም ማንበብ እንደሚነበበው ጉዳይ ማንንነትን ከማዳበር ይልቅ ማንነትን ነጥቆ ማንም ያደረጋቸው የትየለሌ ናቸው …ማንበብ ባዶም ሰው ያደርጋል !!

ሰው ነፃ ፍጡር ነው ከፈለገ ያንብብ ካልፈለገ ዝም ብሎ ይኑር!! በበኩሌ መፃፍም ማንበብም ከሚያዘወትሩ ሰወች ይልቅ ፊደል ያልቆጠሩ ሰወች የተሻለ ማንነት ያልተዛነፈ ሰብእና ያልተቃወሰ የሂወት መስመር እንዳላቸው አይቻለሁ ማንበብን የማንነት መለኪያ የእውቀት ጥግ አድርገው የሚያቀርቡ ሰወች የሚነግሩን ያነበቡትን ነው !! ከገጠር የመጣውን መፅሃፍ አዟሪ ጠጋ ብላችሁ ብታዋሩት ከመፀሃፉ ደራሲ የተሸለ ሰብእና ሊኖረው ይችላል ካላመናችሁ ሞክሩት …አዟሪው ልቡ ንፁህ ነው !!

አንዳንድ ቦታ የሚለጠፉ ማስታወቂያወች ይገርሙኛል ‹‹የማያነብ ሰውና ረግቶ የቆመ ውሃ አንድ ናቸው›› ይልሃል …ካላነበብክ ለውጥ የለም እድገት የለም ስልጣኔ የለም ሂወት ይሰለቻል ለማለት ነው ሂወት እጅ እጅ ብሎት በተገናኘ ቁጥር መጠጥና ማኪያቶውን እየጨለጠ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ ? ›› የሚለው ግን ማነው ?…ያነበበው!! እውነቱን ለመናገር አንባቢው ማንበብ ሰልችቶታል አንብቡ የሚሏችሁ ብዙወቹ ማንበብ ካቆሙ ዘመን የላቸውም ካላመናችሁ አንድ መፅሃፍ ሲያነቡ ተመልከቷቸው ስህተት እና እንከን እንጅ የመፅሃፉን ጭብጥ ሲያሳስባቸው አታገኟቸውም ማንበብ የተጣመመን የማያቃና እንከን መለቃቀም ከሆነ የአገሬ ሃሜተኛ ምናለኝ !!

ዝም ብለው ወቃሽ ነገር ናቸው አማራሪ …. ዋናው ነገር ግን ማንበብ በዘመቻም በዛቻም ሳይሆን በነብስ መሻት ብቻ መከወን ያለበት የሂወት አንድ ክፍል ‹ብቻ› ነው !! ስላላነበብክ እንደሚሉት ‹ብዙ አይቀርብህም› ባዶም አትሆንም …. ስላነበብክም ማንበብ በራሱ ተአምር አይደለም …ከማወቅ ከፍለህ ታውቃለህ እንዲል ቃሉ መቸም ሙሉ አትሆንም … እንደውም ከስጋ እየሸሸህ ቃል ትሆናለህ …ስጋም ያለቃል ቃልም ያለስጋ ሙላትን ያመጣል ማለት ዘበት ነው!! አንድ አባባል ትዝ አለኝ

ብዙ ስታነብ
ብዙ ታውቃለህ
ብዙ ስታውቅ
ብዙ ትረሳለህ
ብዙ ስትረሳ
ምንም አታውቅም !!
<<ምንም አታውቅም ስለዚህ አንብብ >>የሚልህ አንባቢ ሲያድግ አንተን ነው የሚሆነው !!

በመጨረሻም የምልህ ምን መሰለህ አንብብ የሚሉህን እርሳቸውና አንብብ! እምቢ! ካልከኝ ያልኩት ገብቶሃል!!

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s