የዘገየ የሚመስል ግን አሁንም፣ ለወደፊትም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ፤

ወንጀል እየተሠራ መሆኑን መንግሥት እያወቀ እንዴት ዝም ይላል? አንድ ሰው ወንጀል በመሥራት ሲጠረጠር (ሲታወቅ) ወዲያውኑ ለሕግ መቅረብ አለበት፡፡ አለዚያ ግን ይህ ሰው ማንም አላየኝም ብሎ ወይም የልብ ልብ ተሰምቶት፣ መረን እንደተለቀቀ ሁሉ እንደፈለገ ይፈነጫል፡፡ በርግጥም ይህ ነገር በተደጋጋሚ በግልፅ ታይቷል፡፡ (ለምሳሌ በፊት የከተማ መሬትን በመውረር፣ የአራጣ አበዳሪዎች ጉዳይ፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ ደግሞ አሁን በመታየት ላይ ያለው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች የሙስና ቅሌት፣ ተጠርጣሪዎቹ ብዙ ርቀት ከተጓዙ በኋላ ነበር መንግሥት እነሱን ለፍርድ ሊያቀርብ ደፋ ቀና ያለው፡፡) መንግሥት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ይህንን ያህል ወንጀል ሲሰሩ እያየ እንዴት ዝም ብሎ ኖረ? ስለማያውቅ? መረጃ ስለሌለው? የማይሆን የማይመስል ነገር ነው፡፡ በርግጥ ምንም ሳያጣራ ማሰር ተገቢ አይደለም፡፡

እያንዳንዱ ሰው በወንጀል እንደተጠረጠረ ለሕግ ቢቀርብ ኖሮ ያ ሰው ብዙ ጉዳት ሳያስከትል ሕግ ይከለክለው ነበር፡፡ ይህ ሰው ዝም ከተባለ እርሱ ራሱ ብዙ ጥፋት ያመጣል፣ ሌሎችን ወደ እርሱ በማስጠጋት ወንጀል እንዲሰሩ ያደርጋል፤ ይተባበሩታል፡፡ በኋላም ወንጀል ትልቁን ሥር ሰዶ ለመንቀል አዳጋች ይሆናል፤ በዘመቻ ለማስወገድም ያዳግታል፡፡ ብዙ ጥፋት ከደረሰ በኋላ ለፍርድ ማቅረብ በርግጥ ዝም ብሎ ከሚቀር ይሻላል፡፡ ለፍርድ ቢቀርብም እንኳ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ያለው ጣጣ ብዙ ነው፡፡

ተጠርጣሪን አድኖ ለመያዝ የሚወጣውን ነገር አስቡት፣ ከተያዙ በኋላ ለሕግ ፊት ሲቀርብ መንግሥት/ዐቃቢ ሕግ/ የሚደርስበት መከራ (ማስረጃ ይጠፋል፣ ይሰወራል፣ ይሸሻል…) አስቡት፣ ፍ/ቤቶች የሚገጥማቸውን ያንን ትልቅ መዝገብ/ክስ ለመመልከት የሚጠፋው ጊዜ … እስከ ውሳኔ ድረስ፣ (የፍ/ቤት የተራዘመ ሥነ-ሥርዓት ደግሞ በራሱ ትልቅ ፈተና ነው)፡፡ ለምሳሌ አሁን እየታየ ባለው የገ/ጉ/ባለሥልጣን ሠራተኞች የእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ብቻ 60 ገጽ ነው፡፡ በሌሎች ተከሳሾች ላይ ያለውን ደግሞ አስቡት፡፡ (በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት የሚያደርግ ሰው ካለ ጥሩ ሥራ ሳይፈጠርለት አይቀርም፡፡) በአጠቃላይ የዘመቻ ሥራ ያስመስለዋል፡፡ የዘመቻ ሥራ ደግሞ ውጤቱ ….፡፡ ሥር የሰደደውን ወንጀል ደግሞ ለመንቀል እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የሕዝቡ እምነት ይሽመደመዳል፡፡ ሕዝብ የማያምነው መንግሥት ደግሞ የትም አይደርስም፡፡ ስለዚህ ወንጀል ሰሪዎችን ከሥር ከሥር ለሕግ ማቅረቡ የዚህ ሁሉ መፍትሔ ይመስለኛል፡፡

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s