ውል በኢትዮጵያ

እንዴት ሰነበታችሁ ውድ ኢትዮጵያዉያንና ኢትዮጵያውያት፤

አንድ ታላቅ ፕ/ር ስለ ኢትዮጵያ የውል ሕግ በተመለከተ የጻፉትን ካነበበኩ በኋላ የተሰማኝን ነገር ላጫውታችሁማ፤ ጨዋታውን ዛሬ ላጫውታችሁ እንጅ ነገሩንስ (የሥራ ግዴታ ስለሆነ) ካነበብኩት ሁለትና ሦስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ለማንኛውም ጨዋታዬን ልጀምር፣ ታዲያ ዓይንና ጆሯችሁን አትንፈጉኝ፡፡

እኒህ ምሁር የኢትዮጵያን ፍትሐ ብሔር ሕግ ያረቀቁት ፈረንሳዊዉ ፕ/ር ሬኔ ዳዊት ናቸው፡፡ ፕ/ር ሬኔ በ1955 ዓ.ም የጻፉት “ፍትሐ ብሔር ሕግ ለኢትዮጵያ: ….” በሚል አርዕስት ሲሆን ፍትሐ ብሔር ሕግ ለኢትዮጵያ ለምን እንደተመረጠና እንደሚያስፈልግ፣ ስለ እርሳቸው የፍትሐ ብሔር ሕግ የማርቀቅ ዘመን እንዲሁም ስለ ነበረው ሥርዓትና ሁኔታ፣ ስለ ፍትሐ ብሔር አንቀጾች አመጣጥ፣ ከየትኛው ምንጭ እንደተቀዱ … የጻፉት ነው፡፡ በዚህ ጽሑፋቸው በፍትሐ ብሔር ስለተካተተው የውል ጽንሰ ሐሳብ እንዲህ አሉ፤ “….በፍትሐ ብሔር ሕጉ ስለ ውል የተነገረው ነገር በሙሉ አዲስ ነው፤ ምክንያቱም የትናንት ኢትዮጵያውን ስለ ውል ጽንሰ ሐሳብ ምንም የሚያዉቁት ነገር የለምና….” የሚል ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በነገራችን ላይ ይህን አባባላቸውን ፕ/ር ቺቺኖቪችም ይጋሩታል፤ እርሳቸውም በኢትዮጵያ ውስጥ ልማዳዊ/ባሕላዊ የውል ሕግ የለም ይሉናል፡፡

ስለ ውል ሕግ አረቃቅ የጻፉትን ነበር ከላይ ቀንጨብ አድርጌ ያቀረብኩት፡፡ ነገር ግን ይሕ በተለይ ስለ ውል ህግ ያስቀመጡት ዐረፍተ ነገር እንዴት ዓይነት ተአምር ነው ያሰኛል፡፡ ፕ/ሩ ከሌሎች ስራዎቻቸው ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ ሕግጋት ብዙ ነገር አንብበዋል፣ ጽፈዋልም፣ በንጽጽራዊ ሕግም የታወቁ ምሁር ነበሩ፡፡ ስለ ፍትሐ ነገሥቱ በደንብ አድርገው ያውቃሉ፣ ጽፈዋልም፤ ለነገሩ ቀዳሚው የፍትሐ ብሔሩ አገራዊ ምንጭ ማን ሆነና? ታዲያ ስለ ውል ያንን ነገር መጻፍ እንዴት ግራ አያጋባም ትላላችሁ ሰዎች? እኔ ግን እንዴት እንደተረዱት እስከ አሁን ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ስለ ውል ምንም አያውቁም ማለት ምን ማለት ነው? (ይህችን ዐረፍተ-ነገር ሃበሻዊ ቁጭት ልጨምርባት እንዴ? አይይይይ …. የለም ለጊዜው ቁጭቷን ገሸሽ ላድርጋት)

ይህን ነገር ሳነብበው ብዙ ጊዜ ጥያቄ ይመጣብኛል፤ ‹ኢትዮጵያውያን ይህን ያክል ዘመን ሲኖሩ ውል (ወይም ልማዳዊ የውል ሕግ) አያውቁም› ማለት እንዲያው በትንሹ እንኳ ዕቃ ሳይሻሻጡ ቀርተው ነው ወይ የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ሕግስ (የተጻፈም፣ ያልተጻፈም፣ መንግሥት ያወጀውም፣ የልምድም) ሳይኖራቸው ቀርቶ ነው የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ይህንን በማስረዳት አልደክምም፤ ምክንያቱም ከማስረዳት ይልቅ ይህንን አለማወቅ በራሱ ድካም ስለሆነ፡፡

ደግሞ ምንም የሚገዙበት/የሚተዳደሩበት ሕጉ ይለያይ እንጅ ይህንን ግንኙነታቸውን የሚገዛ ሕግ መኖሩ ደግሞ አይቀሬ ነው፡፡ አይካድምም! ፍትሐ ነገሥትን ማንሳት በራሱ በቂ ነው፡፡ አኔም ጉዳዩን ከዚህ አንጻር ተመልክቼዋለሁ፡፡ ፍትሐ ነገሥቱ በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያውያንን (በተለይ የክርስቲያኑን) የሃይማኖት ሥርዓት፣ ልምድ፣ አኗኗር፣ ባሕል፣…የነገሥታቱንም የሕዝባውያኑንም በመቀየርና ተጽዕኖ በማሳደር ወደር የለውም፤ እስከ አሁን ድረስ፡፡ ወደ ፊትም አይቀርም፡፡ የዛሬው ዘመን ሥርዓት፣ ልምድ፣ ባሕል፣ አኗኗር የፍትሐ ነገሥቱና የሌሎች መሰል ድርሳናት ውጤት ነው፡፡ ወደ ፊትም ይህ ተጽዕኖው የሚቀጥል (ይመስለኛል) ነው፡፡

በዚህ ሕግ ታዲያ ስለ ውል በተለይ ብዙ ተብሏል፤ ዝርዝሩን ማንበብ ለአንባቢ ልተወውና ጥቂት አንቀጾችን ከፍትሐ ነገሥቱ ልጠቁማችሁ፡፡

አንቀጽ 27፡ ስለ ብድርና ስለ ዋስትና ስለ መያዣ ስለ መጋቢነት

አንቀጽ 28፡ እንደ ልብስና እንደ እንስሳት ሌሎቹንም ስለ መሰሉ

አንቀጽ 29፡ ገንዘብን አደራ ስለማስጠበቅና ስለመሰለውም

አንቀጽ 33፡ ስለ ዋጋና ስለመገበያት ስለሚከተላቸውም

አንቀጽ 36፡ ቤትን ስለ መከራየትና ለመሬት ገንዘብን ስለመስጠት

አንቀጽ 37፡ ሕንጻን ስለ መሥራትና ስለሚከተለውም

አንቀጽ 38፡ ስለ ብድር

እና ሌሎች የፍትሐ ነገሥቱ አንቀጾች ስለ ውል አብራርቶ ይናገራል፡፡ እንግዲህ እነዚህን አንቀጾች ብቻ እንኳ ብናስተውል ኢትዮጵያ እነዚህን የውል ዓይነቶች በተመለከተ ከ15ኛው መ/ክ/ዘ ጀምሮ የተጻፈ ሕግ እንዳላት እንረዳለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕ/ር ሬኔ ዳዊት የጻፉት ግን መሠረት የሌለው ነው እላለሁ፡፡

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s